እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር፥ በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና። ቆላስይስ 1፥19
ምሥራቃውያን ኦርቶዶክሳውያን በሰሙነ ሕማማት የሚገኙት ን ቀናት ታላቁ ሰኞ፥ ታላቁ ማክሰኞ (Great Monday, Great Tuesday ) እያሉ ይጠሩአቸዋል። በዚያ ልማድ የእኛም ቀዳሚት ሥዑር ታላቂቱ ቅዳሜ በመባል ትታወቃለች። በዚህ እለት አባቶቻችን መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞንን በዜማና በንባብ በመጸለይ፥ በቤተ ክርስቲያንና በክርስቶስ መካከል ያለውን ልዩ የሆነ ፍቅር በማሰብ ክርስቶስ የአዳምን ልጆች ሁሉ ከሲኦል ነጻ እንዳወጣ፥ በአካለ ነፍስ ወደሲኦል ወርዶ በዚያ ላሉት ነጻነትን እንደሰበከ ይናገራሉ፤ ያበሥራሉ፤ የኃጢአት የጥፋት ውሃ እንደጎደለ፥ ዓለም እንደዳነ ለማብሰር ቄጤማ ያድላሉ። ይህም ኖህ ከጥፋት ውሃ በዳነ ጊዜ ርግቡዋን ሲሰዳት ቄጤማ ይዛ መምጣትዋን የሚያመለክት ነው።
Saturday, April 3, 2010
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
-
የጌታን ልደት ከማክበራችን በፊት ያሉት ሦስት ሳምንታት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ታላቅ ሥፍራ አላቸው። ከዘጠኙ ንዑሳን የጌታ በዓላት መካከል የሚቆጠሩም ናቸው። የመጀመሪያው ሳምንት ስብከት፥ ሁለተኛው ብርሃን፥ ሦስተኛው ...
-
የአባቶቼ አምላክ፥ አምላከ ቅዱሳን አምላከ አበው ልዑል እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ከፍ ካሉት ሁሉ በላይ ከፍ ያልህ ነህ፤ ሥራህ ከአእምሮ በላይ ነው። ኃይል ከመነገር በላይ ነው። ኃጢአተኛ እና በደለኛ የሆንኩትን እኔን ልጅ...
-
የቅዱስ ጳውሎስ አጭር ታሪክ ስለ ጳውሎስ ማንነት በጥልቀት የምናገኘው ሉቃስ ከጻፈልን ከሐዋርያት ሥራ እና ከራሱ ከቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት ነው። 1. በጠርሴስ ተወለደ ቅዱስ ጳውሎስ በአሁኑ ዘመን በ...
No comments:
Post a Comment