ወንጌልና ተጽዕኖ 1:1-10
1-2 በኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታንም ባነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆነ እንጂ ከሰዎች ወይም በሰው ያልሆነ ጳውሎስ ከእኔም ጋር ያሉት ወንድሞች ሁሉ፥ ወደ ገላትያ አብያተ ክርስቲያናት፤3 ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።4 ክፉ ከሆነ ከአሁኑ ዓለም ያድነን ዘንድ እንደ አምላካችንና እንደ አባታችን ፈቃድ ስለ ኃጢአታችን ራሱን ሰጠ።5 ለአብ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን። 6 በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤7 እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ።8 ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።9 አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።10 ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም።
ሀ. የመልእክቱ ምክንያት
ለ. የጳውሎስ የሥልጣኑ ምንጭ
<< በኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታንም ባነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆነ እንጂ ከሰዎች ወይም በሰው ያልሆነ ጳውሎስ>>
ሐ.የገላትያ አብያተ ክርስቲያናት የተቀበሉት ጸጋ
- ወንጌል ጌታ ኢየሱስ ከርስቶስ ነው:: << በኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታንም ባነሣው በእግዚአብሔር አብ ...>>
- ወንጌሉ ጸጋና ሰላም ነው:: << 3 ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።>>
- ወንጌል ከክፉው ዓለም ሊያድነን ራሱን አሳልፎ ስለሰጠው ስለ ክርስቶስ ነው። << ክፉ ከሆነ ከአሁኑ ዓለም ያድነን ዘንድ እንደ አምላካችንና እንደ አባታችን ፈቃድ ስለ ኃጢአታችን ራሱን ሰጠ። >>
- ወንጌሉ ወደ ክርስቶስ ጸጋ የሚጠራን ነው። << በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ....
መ. የገላትያ አብያተ ክርስቲያናት የገቡበት ወጥመድ አስፈሪነት
- በክርስቶስ ጸጋ ከጠራቸው ወንጌል ወደ ልዩ ወንጌል ፈጥነው አልፈዋል። << 6 በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤>>
- ይህ ልዩ ወንጌል ወንጌል ያይደለ የተጣመመና ከክርስቶስ ጸጋ የሚያናውጥ ነው። <<7 እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ።>>
- ይህ ልዩ ወንጌል ወደ እርግማን የሚወስድ ነው። << ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።9 አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን። >>
ሠ. የጳውሎስ ቁርጠኝነት
ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም።
No comments:
Post a Comment