በዚህ በአገረ አሜሪካ ከሚገኙት ታዋቂ የአሜሪካ ፉት ቦል ቡድኖች መካከል (ሶከሩን አይደለም) አንዱ ኮልት ነው። ታዲያ ከሰሞኑ የአሰልጣኙን በሉኪሚያ ካንሰር መታመም ተከትሎ ሠላሳ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች፥ የዋናውን አሰልጣኝ በኪሞ ቴራፒ ውስጥ ማለፍ ለማበረታት ጸጉራቸውን ተላጭተው ነበር። ከሁሉ ልቤን የነካው ሁለት የቡድኑ አድማቂ (cheerleaders) እህቶች አብረው ጸጉራቸውን መላጨታቸው ነው። ቅዱስ መጽሐፍ «ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፥ ከሚለቅሱም ጋር አልቅሱ።» ይህንን ታላቅ ድርጊት ደግሞ ራሱ ቤዛችንና መድኅናችን አድርጎታል። በኃጢአት ፍላጻ ተነድፎ ለሞት የተሰጠውን የሰው ልጅን ከወደቀበት ሐዘቅት ያድነው ዘንድ፥ ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እኛን መስሎአል። የቤተ ክርስቲያን ጥሪዋና ድምጽዋ በውጭ ላሉት ሊደርስ ያልቻለው፥ እኛ « በውስጥ» ያለነው ብዙ ጊዜ የምንጨነቀው ራሳችን ከሌሎች ለመለየት እንጂ ከተጠቁት፥ ከተገፉት፥ ልባቸው ከተሰበረውና ግራ ከገባቸው ጋር አንድ ለማድረግ አይደለም። የኮልት ቡድን አባላት ድርጊት ታላቅ ትምህርት ያስተምረን ይሆን?
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
-
የጌታን ልደት ከማክበራችን በፊት ያሉት ሦስት ሳምንታት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ታላቅ ሥፍራ አላቸው። ከዘጠኙ ንዑሳን የጌታ በዓላት መካከል የሚቆጠሩም ናቸው። የመጀመሪያው ሳምንት ስብከት፥ ሁለተኛው ብርሃን፥ ሦስተኛው ...
-
የአባቶቼ አምላክ፥ አምላከ ቅዱሳን አምላከ አበው ልዑል እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ከፍ ካሉት ሁሉ በላይ ከፍ ያልህ ነህ፤ ሥራህ ከአእምሮ በላይ ነው። ኃይል ከመነገር በላይ ነው። ኃጢአተኛ እና በደለኛ የሆንኩትን እኔን ልጅ...
-
የቅዱስ ጳውሎስ አጭር ታሪክ ስለ ጳውሎስ ማንነት በጥልቀት የምናገኘው ሉቃስ ከጻፈልን ከሐዋርያት ሥራ እና ከራሱ ከቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት ነው። 1. በጠርሴስ ተወለደ ቅዱስ ጳውሎስ በአሁኑ ዘመን በ...
No comments:
Post a Comment