Monday, March 11, 2013

ጸሎተ ስምዖን ዓምዳዊ (ክፍል 10)


ምዕራፍ ፳፰፤ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥የመንፈሳዊ መነቃቃትን እሳት ስጠኝ። 
ምዕራፍ ፳፱፤ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ስለአንተ አብ አሰምቶ የተናገረ፥ እንዲህም ያለ፥ በእርሱ ደስ የተሰኘኹበት የምወደው ልጄ ይህ ነው። አቤቱ እለምንሃለሁ የድምጽህ ቃል ወደ ጆሮዬ ይግባ፥ ነፍሴንም ያድነው፤ የቃልህን ድምጽ የሚሰማ ይድናልና። የሚያይህም እንዲሁ ይድናልና። መዓዛህን የሚያሸት ይድናል። አንተ ሞት የማያገኘው ሕይወት ነህና። 
ምዕራፍ ፴፤ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በላይህ ላይ የወረደ፥ ሕያውና ቅዱስ የሆነውን መንፈስህን በእኔ ላይ አሳድር። ወደ መሠወሪያህ ይበር ዘንድ፥ በታላቁ ምጽአትህም ይቀበልህ፥ ዝም በማይል አንደበት አንተን እያመሰገኑ ካሉት አእላፋት ከሚሆኑ አላፋት መላእክት ጋር ጋር አንተን ያመሰግንና ይሰግድልህ ዘንድ ለልቤ መንፈሳዊ ክንፍን ስጠው። 
ምዕራፍ ፴፩፤ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ እሳትን ልጥል መጣሁ እንድትነድም እወዳለሁ ያልህ፤ በተሐድሶ አዲስ እስክታደርጋት፥ ከሐሳባት እስክትለያት ድረስ በሕሊናዬ ውስጥ እሳትህን አንድድ። በጨለማ ያሉትን ብርሃን፥ ርኵሳንን ቅዱሳን ልታደርጋቸው ያችን እሳት ከጥምቀት ውኃ ጋር ደመርካት፤ይህችም እሳት የኃጢአትን ሸለፈት (ቍልፈት) ከሰዎች የምትገዝር፥ ያረጁ ልማዶችን የምትቆርጥ ከመለኮት ዘንድ የሆነች እዲስ ልብን የምትሰጥ የመንፈስ ቅዱስ ሰይፍ ናት። . . . 

1 comment: