Read in PDF
ነአምን በ፩ አምላክ እግዚአብሔር አብ አኃዜ ኵሉ ገባሬ ሰማያት ወምድር ዘያስተርኢ ወዘኢያስተርኢ
ሁሉን በያዘ ሰማይንና ምድርን የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን።
እስከ አሁን እግዚአብሔር በገለጠልን መጠን ስለ አንድነቱና ስለሦስትነቱ ማለትም ስለምሥጢረ ሥላሴ ተምረናል። ምሥጢረ ሥላሴ ማለት የእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት እንደሆነ፥ ይህም ማለት አንዱ እግዚአብሔር ሦስት እኔነት ሦስት እኔ ነኝ ባይ አካላት እንዳሉት አይተናል። የእግዚአብሔር የሦስትነት ስሙም አብ ወልድ መንፈስ ነው። እርስ በእርሳቸውም የሚገነዛዘቡበት የኵነት ስማቸውም ልብ፥ ቃል እስትንፋስ ነው። ኦርቶዶክሳውያን አባቶች ለዚህ ትምህርታቸው መሠረት ያደረጉት የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላትንና አገላለጾችን ነው።
ሆኖም ከዚህ በፊት እንዳልነው ምሥጢረ ሥላሴን ገልጦ ለመጨረስ መሞከር አይቻልም። ወይም የአባቶቻችንን አገላለጥ ለመጠቀም ውቅያኖስን በዕንቁላል ቅርፊት ጨልፎ ለመጨረስ እንደመሞከር ነው። ባለፉት ክፍሎች ያነሣናቸው ነጥቦች ለጊዜው ደብዘዝ ቢሉብን ብዙ አንጨነቅ፤ የበለጠ ስለ ራሳችን ማንነት ባየን ወቅት የበለጠ ስለመዳናችን ስንወያይ፥ የእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት ግልጥ ይሆንልናል። ይህ ግን እምነታችን ነው። « በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን። አንድ ሲሆኑ ሦስት ሦስት ሲሆኑ አንድ ናቸው። በአካል ሦስት ናቸው። በመለኮት በአገዛዝ በሥልጣን አንድ ናቸው። አብ እኛን ከመውደዱ ከታላቅ ፍቅሩ የተነሣ አንድያ ልጁን ወልድን ሰዶልናል። ወልድ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰው ሆኖአል። በመሰቀል ተሰቅሎ ሞቶ ተነሥቶ አድኖናል። አሁን በክብር አርጎ በአባቱ ቀኝ ተቀምጦአል። መንፈስ ቅዱስ ቀድሞ ፍጥረትን ያስተናበረ ሕይወትና ውበት የሰጠ (ዘፍጥረት 1፥2) አሁን ደግሞ በክርስቶስ የተከናወነው የማዳን ሥራ እውን እንዲሆን በሞተው ሕይወታችን ውስጥ ሕይወት ሰጥቶናል። ቀድሶናል።
ሰማይንና ምድርን የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ ፤
ሀ. ሥነ ፍጥረት
አባቶቻችን ይህን የሚታየውንና የማይታየውን ዓለም ሰማዩንና ምድሩን እግዚአብሔር የፈጠረበትን መንገድ በሃይማኖት (በሳይንስ አይደለም) ያጠኑበት ትምህርት ሥነ ፍጥረት ይባላል። እነቅዱስ ባስልዮስ፥ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ እና ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይህን ያስተማሩበት ሄክሳሜሮስ ወይም አክሲማሮስ በሚል ይታወቃል። ስድስቱን የፍጥረት ቀናት የሚያመለክት ነው። ዛሬ ሳይንሱ ከፍተኛ ርቀትና ጥበብ ውስጥ ባለበት ወቅት የአባቶቻችንን የሥነ ፍጥረት መንገድ የምናጠናው ለምንድነው ተብሎ ይነሣ ይሆናል። ዛሬ ከመቼውም በበለጠ ስለ ፍጥረት እያየን ባለንበት ወቅት የእግዚአብሔርን ታላቅነት የኑሮአችንና የምርምራችን ማዕከል ልናደርገው ይገባል።
ስለፍጥረት ስንመምረምር የሚከተሉትን ነጥቦች ልንረዳ ይገባል።
1. እግዚአብሔር ዓለማትን የፈጠረው በሦስትነቱ ነው።
እግዚአብሔር አብ በልብነቱ አስቦና ፈቅዶ ዓለምን ልፍጠር ብሎ አሰበ፥ ፈቀደ፥ ፈጠረ (ራዕ 4፥10_11
እግዚአብሔር ወልድ ዓለም የተፈጠረበት ቃል ነው። እግዚአብሔር አብ ዓለምን የፈጠረው በቃሉ ነው። ዮሐንስ በወንጌሉ እንደነገረን ሁሉ በእርሱ (በቃል) ሆነ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ (ያለ ቃል) አልሆነም። ዮሐንስ 1፥3። ቅዱስ ጳውሎስም ስለ ወልድ ሲናገር « በሰማይና በምድር በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል።» ቆላ 1፥16።
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለፍጥረቱ መልክና ቅርጽ፥ ሕይወት የሰጠ ነው። ሙሴ የፍጥረትን ታሪክ ሲጽፍ « « የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር» ይለናል። ዘፍጥረት 1፥2።
2. እግዚአብሔር ዓለማትን የፈጠረው በሉዓላዊ ፈቃዱ ነው።
እግዚአብሔር ዓለማትን የፈጠረው ማንም አስገድዶት አይደለም። ወይም ለሕልውናው አስፈልጎት አይደለም። ዓለማትን የፈጠረው በፈቃዱ ነው። ራዕ 4፥10