ዶክተር ሊሊያን አልፊ (ትርጉም ቀሲስ መልአኩ ባወቀ)
የሚከተለው መጣጥፍ የግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመን የሆኑ ዶክተር ሊሊያን አልፊ « የሰማይ መጽናናት» በሚለው መጽሐፋቸው ካስቀመጡት ጽሑፍ የተቀነጨበ ነው።
ወደ አልአዛር እንመለስና [ከቤተ ክርስቲያን ታሪክ በትውፊት እንደምንረዳው] ከተአምራታዊ ትንሣኤው በኋላ ለተወሰኑ ዓመታት እንደኖረ፤ በእርሱ ላይ የተከናወነው ተአምራት የጌታን አምላክነት የሚያሳይ ስለሆነ አይሁድ ያሳድዱትና ሊገድሉት ይሞክሩ እንደነበረ እናገኛለን። በመጨረሻም ለሁለተኛ ጊዜ አርፎ ዓለም ሳይፈጠር ወደ ተዘጋጀለት ዘላለማዊ ቦታ ሄዶአል። በዚያም በሁለተኛው ተአምር ምክንያት የዘገየበትን እውነተኛ እረፍት አግኝቶአል። ለአላዛር ምርጫ ብንሰጠው ኖሮ [ቅዱስ ጳውሎስ እንደመረጠው] እንዲህ ይለን ነበር፦ « የእኔ ፍላጎት እንኳ መሄድ ከጌታዬም ጋር መሆን ነበር ነገር ግን እኅቶቼን ለማጽናናትና የጌታን አምላክነት ለማሳየት በእኔ ላይ የጀመረውን ሥራ ለመፈጸም በሥጋ እንደገና ተመልሻለሁ።» አሜን ።
No comments:
Post a Comment