የምግብን ነገር ወደኋላ ማድረግ ቀላል ነገር ነው። ቍርስን መተው ፥ ጤናማ ያይደለ ነገር መቀማመስ፥ በጥድፊያ፥ በመንገድ ላይ ሆኖ ወይም በቢሮ መብላት የተለመደ ነው። ፈታኙ የቢሮ የልደት ኬክ ሳይጠቀስ ነው።
ታዲያ ምን እናድርግ? በመጀመሪያ ሰውነታችሁ ኃይል እንዲያገኝና ለውሎአችሁ ጉልበት እንዲሰጣችሁ በቂ ቁርስ ማግኘታችሁን እንዳትዘነጉ። በዕለቱ ስለምትመገቡት ምግብ አስቀድማችሁ ዕቅድ አውጡ። ዕቅድ ማውጣት ከመቅሰስ መቸርቸሪያ ማሽኖች ( Vending machines) እና የይድረስ ይድረስ ምግቦች ( fast food.) ራቅ እንድሉ ያደርጉአችኋል። ለመቅሰስ ሊሆኑ የሚችሉ ምግባ ምግቦች በ ለምሳሌ አትክልት፥ ቅጠላቅጠሎች ጥራጥሬዎች (በተለይ የለውዝ ዝርያዎች) በአጠገባችሁ ይሁኑ፤ ሆኖም ምግባችሁን ከጠረጴዛችሁ አጠገብ አርባ አርቁት። በተቻለ መጠን የምትበሉትን እያስተዋላችሁ እንጂ በችኮላ ወደ አፍ በመውሰድ አትብሉት።
No comments:
Post a Comment