Wednesday, November 20, 2013

አልቃሹም፥ አስለቃሹም፥ ማልቀሻውም . . .



በአገሬ በኢትዮጵያ አንድ የቆየ ልማድ አለን። አንድ ታላቅ ሰው ይሞትና ለቀብሩ ዘመድ አዝማድ ከሩቅ ቦታ ላይደርስ ይችላል። በዚህ ላይ የቆላው ደጋ መውረድ ስለማይችል። ቀብሩ ከተፈጸመ በኋላ በቀጠሮ ይገናኛል። ለለቅሶ። 
ለለቅሶም ለጩኸትም ዛሬ ሎስ አንጀለስ ላይ ከየቦታው ተገናኝተን ነበር። 
ለዚያች እህቴ፤ ለውርደቷ፥ ለስቃይዋ፥ ለሕመሟ. . . ጮኽን 
ለዚያ ለወንድሜ፤ የአረቢያ ምድረበዳ ደሙን ለጠጣው. . . አለቀስን 
ለእኛም ለሁላችን፤ አገር ሳናጣ፥ በረከት ሳያንሠን እንዲህ ለሆንነው . . . ተላቀስን 
ለቅሶ የሩቅ ዘመድን፥ የናፍቅነውን ያገናኛል . . .  ወንድሞቻችንን እህቶቻችንን ከወደ አሥመራ . . . ተያይዘን እሪ አልን። 
እሥመራ መድኃኔ ዓለም ትዝ አለኝ፤ ወንድሞቼና እህቶቼ 
ሁላችን አለቅስን፥ ሁላችን አስለቀስን፥ ስለሁላችን አለቀስን 

ስለእህት ስለወንድም፤ ስለአገር ስለወገን፤ ስለክብር ስለሕይወት. . . . ስለራስ አነባን። እግዚአብሔር ጽናቱን ይስጠን። 

No comments:

Post a Comment