« ትህትና» ወይም « ራስን ማዋረድ» የባሪያ ባሕርይ ወይም ሥነ ምግባር እንጂ የኵሩዎቹ የሮም ዜጎች ባሕርይ ተደርጎ አይታሰብም ነበር። በዚህም የጥንታዊት ግሪክ የሞራል ሊቃውንት « ትህትና» የዝቅተኛ መደብ ኅብረተሰብ ባሕርይ እንደሆነ አድርገው ይናገሩ ነበር። « ትሕትና» የሚለው ቃል ተትሕተ፥ ተዋረደ፥ ዝቅ አለ፥ ወደታች አለ የሚል ነው። ለዚህ ቃል ምንጭ የሆነው የግሪኩ ሥረወ ቃል « ታፔይኖ የሚለው ቃል ነው። ትርጉሙ « ተራራ መደልደል» ማለት ነው። ይህም ክርስቲያናዊ የሆነን ትሕትና ትክክለኛ ትርጉም ያመለክተናል። ይህም ከፍ ያለ ሰው ራሱን ዝቅ ለማድረግ መወሰን ክብርን ማንነትን መተውን የሚያመለክት ነው። በመሆኑም ትሕትና ለራስ አክብሮትን የማጣት በሽታና የዝቅተኝነት ስሜት መገለጫ ሳይሆን ሌሎችን ለማገልገልና እነርሱን ለመጥቀም ቦታን መተው የሚያመለክት ነው።ይኸውም ሊታወቅ ራሱ ክርስቶስ ከፍ ካሉት ከፍ ያለ የእግዚአብሔር ልጅ ሲሆን ትሑት ሆኖ ራሱን አዋርዶ ሌሎችን አገልግሎአል። ( ማቴዎስ 11፥29)
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
-
የጌታን ልደት ከማክበራችን በፊት ያሉት ሦስት ሳምንታት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ታላቅ ሥፍራ አላቸው። ከዘጠኙ ንዑሳን የጌታ በዓላት መካከል የሚቆጠሩም ናቸው። የመጀመሪያው ሳምንት ስብከት፥ ሁለተኛው ብርሃን፥ ሦስተኛው ...
-
የአባቶቼ አምላክ፥ አምላከ ቅዱሳን አምላከ አበው ልዑል እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ከፍ ካሉት ሁሉ በላይ ከፍ ያልህ ነህ፤ ሥራህ ከአእምሮ በላይ ነው። ኃይል ከመነገር በላይ ነው። ኃጢአተኛ እና በደለኛ የሆንኩትን እኔን ልጅ...
-
የቅዱስ ጳውሎስ አጭር ታሪክ ስለ ጳውሎስ ማንነት በጥልቀት የምናገኘው ሉቃስ ከጻፈልን ከሐዋርያት ሥራ እና ከራሱ ከቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት ነው። 1. በጠርሴስ ተወለደ ቅዱስ ጳውሎስ በአሁኑ ዘመን በ...
No comments:
Post a Comment