አንድ ወዳጄ ጠጋ ብሎ አንድ ቅር የሚለውን ነገር ነገረኝ፤ በጊዜ ቅዳሴ ስለሚነበቡት ምንባባት። ወዳጄ በመጀመሪያ የጠየቀኝ ጥያቄ እነዚህ በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡት የቅዱሳት መጻሕፍት ምንባባት አስፈላጊ ናቸው ወይ? የሚል ነው። እንዴታ አልኩት። እርሱ ግን አሁንም በመልሴ ሳይረካ « እናንተ ካህናቱ ግን የምታስተላልፉት መልእክት ይህን አይመስልም!» አለኝ። « እንዴት?» አልኩት። እርሱም « መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ መጻሕፍት አሥራው መጻሕፍት ብላ ቤተ ክርስቲያን አክብራ ብትጠራውም። እናንተ ግን ገና ምዕራፍና ቁጥሩን አንባቢው ተናግሮ ሳይጨርስና ወደ ምንባቡ ሳይዘልቅ « ቅዱስ» ብላችሁ መርገፉን ማዜም ትጀምራላችሁ። ለመሆኑ መርገፉ ነው የሚበልጠው ወይስ ንባቡ ነው የሚበልጠው» አለኝ።
የዚህ የወዳጄን ጥያቄ ሰሞኑን አንድ በአገልግሎት የኔው የቅርቤ የሆነ ዲያቆንም ጠይኸንኑ ደግሞ ጠየቀኝ። በእነዚህ በሁለቱ ወዳጆቼ ማሳሰቢያ በኩል እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለእኔ ተናግሮኛል ብዬ አስባለሁ። በጊዜ ቅዳሴ የሚነበቡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ትኩረት ስለማይሰጣቸው አብዛኛው ሰው ምንም ቦታ አይሰጣቸውም። ቤተ ክርስቲያን ግን በዕለቱ ወይም በሰንበቱ ሊነበቡ የሚገባቸው ያለቻቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በግጽው ወይም በመጽሐፈ ግጻዌ ለይታ አስቀምጣልናለች። እነዚህ ምንባባት ተነበው እስከሚያልቁ በአትኩሮት ልንሰማቸው ልንማርባቸው ይገባል እላለሁ። እናንተስ ምን ትላላችሁ?

ይሄ የኔም ጥያቄ ሌላው ቀርቶ ሃይማኖት አበው ሲነበብ በብርሃን ፍጥነት በመሆኑ ከምንሰማው የማንሰማው ይበልጣል የመጽሐፍ ቅዱስ mnbabatma አንዳንዴ የቅዳሴው አካል የሚመስሉበት ሁኔታ አለ...ማለቴ ሲነበቡ በያሬዳዊ መዝሙር መልክ ስለሆን ገእዝ መስሎን ሳንሰማው የምናልፍበት ጊዜ ብዙ ነው
ReplyDeleteበዚህ ሃሳብ እኔም እስማማሎህሸ ሆኖም ግን መእመናኑ ልብ የማይለው በኣበዛኛው ቤቴክርስትያናችን የሚነበቡ ወንጌሎች በግአዝ ስለሚሆን ይመስለኛል።በርግጸኝነት ከኔ ጀመሮ ሳንሰማው ስለምናልፍበት ይሆናል እላሎህ።
ReplyDeleteመጽሐፍ ለሁሉም ጊዜ አለው እንዳለ በጊዜ ቅዳሴ የሚነበቡ መጻሕፍት ጊዜያቸው ይጠበቅላቸው ዲያቆናቱ ና ንፍቀ ካህኑ የተመደበውን ምንባብ አንብበው እስኪጨርሱ ቢጠበቅ፣ ከዚያ በኋላም በስብከት ጊዜ እንደ ቤተክርስቲያኗ መሠረተ ትምህርት መልእክታቸው ቢብራራ ይገባል ብዬ አስባለሁ፡፡ ለዚህ ብቁ ሁለገብ አስተዳዳሪ ሊኖነር ይገባል ፡፡ ይህንን ጊዜ እግዚአብሔር ያቅርብልን፡፡ ቀሲስ እርስዎ ባሉበት ይህንን ያስጀምሩ እላለሁ ፡፡
ReplyDelete