Monday, November 4, 2013

በክርስቶስ የነበረ አሳብ


በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። ፊል 2፥5 
አንድ ጸሐፊ እንደተናገረው « የክርስትና ሕይወት የአድርግና አታድርግ ሕጎች ስብስብ ሳይሆን፥ የክርስቶስ ሕይወት መገለጫ ነው።» ክርስቲያዊ ሕይወትን የምንኖረው ክርስቶስን ስንገልጥ ነው። ታላቁ ክርስቶስን የሚገልጠው ባሕርይ ወይም ክርስቶስ በዚህ ዓለም ላይ ራሱን የገለጠበት ባሕርይ ቢኖር ትህትና ነው።ከጽንስ እስከ መስቀል ድረስ ከቤተ ልሔም ዋሻ እስከ ቀራንዮ መንገዱ የትሕትና ነው። እርሱ ራሱ « እኔ ትሑት ነኝ ብሎ» ተናግሮአል።» (ማቴዎስ 11፥29)  ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን ባሕርይ ልትገልጥ የተጠራች ናት፤ የሚያሳዝነው ነገር የክርስቶስን ባሕርይ በተለይም ትሕትናውን ልትገልጥ የተጠራች ቤተ ክርስትያን የእርሱን ትህትና መናገርን ብቻ ተግባሯ አድርጋ፥ ትሕትናውን መግለጥ ስላልቻለች በዓለም አደባባይ ዛሬ በትዕቢት ትከሰሳለች። ከክርስቶስ ሕይወት መራቅ ማለት ይህ ነው። 

1 comment:

  1. I really love this article. Thank you kesis. Please kesis till us about Jesus.
    May God bless you and your family.

    ReplyDelete