ክርስትና አደጋ ላይ ነው? ከወደ እንግሊዝ የሚሰማው ንግግር ይህን የሚያጸድቅ ይመስላል። የካንትሪበሪ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ሎርድ ኬሪ ክርስትና በተለይ በእንግሊዝ አገር ከአንድ ትውልድ በኋላ እንደሚጠፋ በቅርቡ በተደረገ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።
የሎርድ ኬሪ አስተያየት የተሰማው የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ሲኖዶስ ባደረገው ስብሰባ ላይ በቀረበው ሪፖርት የቤተክርስቲያኒቱ አባላት ቁጥር ክፉኛ ማሽቆልቆሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ ብሔራዊ ተቋም ሆና ለመቀጠል በሚያጠራጥር ሁኔታ እንዳስቀመጣት መነገሩን ተከትሎ ነው።
ስለ ቤተ ክርስቲያናቸው አስደንጋጭ ሁኔታ በመናገር የቀድሞው ሊቀ ጳጳስ ብቻቸውን አይደሉም። የዮርክ ሊቀ ጳጳስ የሆኑ ት ዶክተር ጆን ሴንታሙም አዲስ አባላትን ወደ ቤተ ክርስቲያን መሳብ የቤተ ክርስቲያን ተቀዳሚ ተግባር መሆን እንዳለበትና « ከዚህ ውጭ የሆነው ነገር ሁሉ ቤት በእሳት ተያይዞ የቤት ዕቃን እንደማሳመር ይሆናል ብለዋል።
የዮርኩ ሊቀ ጳጳስ ጨምረውም ቤተ ክርስቲያን ወንጌላዊት ወይም ቅሬታዊት "evangelise or fossilise" እንደምትሆንና ምርጭዋ የእርሷ እንደሆነ ተናግረዋል።
ሎርድ ኬሪ ባደረጉት ንግግር በእንግሊዝ ያሉ ክርስቲያኖች « ድል የተነሱና አንገታቸውን የደፉ» እንደሆኑና ከዚያ መንፈስ ለመውጣት ታላቅ እንቅስቃሴ መደረግ እንዳለበት ተናግረዋል። በተለይም በወጣቶች ላይ ቤተ ክርስቲያን ጊዜዋን ማጥፋት እንዳለባት ተናግረዋል። ስለዚህ ሲናገሩም « በራሳችን ልናፍር ይገባናል። ምክንያቱም በወጣቶቻችን ላይ ያለ የሌለ ኃይላችንን ካላዋልን ከአንድ ትውልድ በኋላ እንጠፋለን፤ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማንም ሰው ስለማይኖር "
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ይህ የእንግሊዝ ሊቃነ ጳጳሳት ንግግር በአብዛኛው በእንግሊዝ አገር ያለውን እውነታ የሚያንጸባርቅ ቢሆንም፥ « ለእኔ ብለህ ስማ» የሚያስብል አባባል ነው። በአንድ በኩል ክርስትና በብዙዎች አዳጊ ዓለማት (ቻይና፥ ሕንድ፥ አፍሪካ በአጠቃላይ) በሚገርም ፍጥነት እያደገ ያለ ሃይማኖት ቢሆንም በሌላ በኩል ግን በአደጉት ዓለማት ( በተለይ በአውሮፓ ) ክርስትና በከፍተኛ ፍጥነት ተከታዮቹን እያጣ የመጣ ሃይማኖት ሆኖአል። ይህም ያለ ምክንያት አይደለም። በአደጉት አገሮች አብያተ ክርስቲያናት እያቀረቡት ያሉት ወንጌል የሞተ ወንጌል ነው። የሕይወት ለውጥ ማምጣት የማይችል። ስለሆነም ወንጌል « የሚያሰለች ማኅበራዊ ትንታኔ» ለታላቅ መንፈሳዊ ለውጥ የሚያነሣሣ፥ ሕይወትን እስከሞት የሚያሰጥ ለውጣዊ መልእክት አልሆነም። የአውሮፓና የአሜሪካ አብያተ ክርስቲያናት ዘመናዊነት ከእጃቸው ላይ የጣለውን ሕያው የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንደገና ማንሳት ይኖርባቸዋል። የዚያን ጊዜ አይደለም በሰንበት ቤተ ክርስቲያን መምጣት፥ ሕይወትን ለታላቅ ተልዕኮ መስጠት በሰዎች ውስጥ ይታያል።
የእኛ አገር ከዚህ ምን እንደምትማር አላውቅም። ለአሁን አደባባዮቻችንን በሰው ተጥለቅልቆአል። አሐዞቻችን ግን አስደንጋጭ ምልክቶች እያሳዩን ናቸው። እንደ ሕዝባችን ቁጥር እድገት የቤተ ክርስቲያናችን አባላት ቁጥር አድጓል ወይ? ቤተ ክርስቲያን በአገር አቀፍ ደረጃ ወጣቱ ትውልድ ላይ ኢንቨስት እያደረገች ነውን? ለሕዝባችንስ የምናስተላልፈው መልእክት የሕይወት ለውጥን የሚጋብዝ ነው? ተወያዩበት
ምንጭ፦ huffington post
No comments:
Post a Comment