ባለፈው ወር የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ኮንግረስ) እሰጥ አገባ ውስጥ ገብቶ በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር ውኃ እንዲበላው ሲያደርግ፥ ዓለም ሁሉ አሜሪካውያን ምን ነካቸው እንዲል አድርጎ ነበር። ከዚህ የሚቀጥለው ምስል ግን ችግሩ ምን እንደሆነ የሚያሳይ ነው።
ይህ ምስል እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1989 የነበረው ኮንግረስ ሁለቱ ፓርቲዎች እንዴት አብረው ይሠሩ እንደነበረ የሚያሳይ ነው። ሪፐብሊካንና ዲሞክራት ለአገራቸው በአንድ አሳብ በመስማማት ይሠሩ ነበር።
ይህ ደግሞ አሁን በሥራ ላይ ያለው ኮንግረስ የሚሠራበት መንገድ ነው። አገር ሲወድቅ እንዲህ ነው ይሉሃል ። ይህን ግራፍ ሳይ ወደ አእምሮዬ የመጣው ሕያው የሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ነው። « እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ሁላ ትጠፋለች፥ እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማም ሁሉ ወይም ቤት አይቆምም።» ማቴዎስ 12፥25 ቶማስ ፍሪድማን እንዳለው እሜሪካ ባንቀላፋችበት በእነዚህ ዓመታት ቻይና ዓለምን እያስገበረች ነው። የኛዋንም ኢትዮጵያን ሳይቀር። ሙሉ ትንተናውን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ
No comments:
Post a Comment