በቂ ውኃ አለመጠጣት የተለያዩ የጤና ቀውሶችን ያስከትላል፤ ከእነዚህ መካከል፦ ራስ ምታት፥ የስሜት መጨቆን ድርቀት ይገኛሉ። በማናቸውም ሁኔታ መልካም ያይደሉ በተለይም ደግሞ ንቁና ምርታማ መሆን በምትፈልጉበት በሥራ ገበታችሁ መፍዘዝ፥ ድካም እና ከመጠን ያለፈ ትኩሳት ሊያጋጥማችሁ ይችላል።
ታዲያ ምን እናድርግ? ምንም ባይጠማችሁ እንኳ ውኃ ዝም ብላችሁ ጠጡ። ስምንት ብርጭቆ ፈሳሽ በቀን ለመጠጣት ዓላማችሁ አድርጉ፤ ቢሮአችሁ ወይም ውጭው የሞቀ ከሆነ ከዚህ የበለጠ ብትጠጡ የተሻለ ነው። የውኃ መጠጫ በቢሮ ጠረጴዛችሁ አቅራቢያ መሆኑ ቀኑን ሁሉ በየጊዜው ለመጠጣት ይረዳችኋል፤ ከዚህ በተሻለ ደግሞ በቢሮአችሁ አካባቢ ወዳለው የውሃ መጠጫ እየሄዱ ቀድቶ መጠጣትን ልማድ አድርጉ። ይህም ሰውነታችሁን ለማንቀሳቀስና ለማርካት ይረዳል። የውሃ ኮዳ ወይም እንደገና ልትጠቀሙበት የምትችሉበትን የውኃ መጠጫ ለመጠቀም ሞክሩ። በዚህም በእንድ ጉዞአችሁ ብዙ ውኃ ልትቀዱበት ትችላላችሁ አካባቢያችሁንም ከብክለት ትጠብቃላችሁ።
No comments:
Post a Comment